በፋና የእርዳታ ተግባራት ...


በፋና የእርዳታ ተግባራት 


1.  ቤተ ክርስቲያናትን ማጠናከር 

የኢኦትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ብዙ ፈተና ቢያጋጥማትም እስከ ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመን ማብቂያ 1966 ድረስ የነበሩት ነገስታት ለቤተክርስቲያን ታላቅ አክብሮት ስለነበራቸው የጠፉት እየተገነቡ በጥሩ ቀጥላለች ። በ1966  ስልጣን የያዘው የደርግ መንግስት ሃይማኖት ጠል ፖሊሲ ስለሚከተል  ያለአግባብ  ህብትዋን  ወርሶ ፓትርያርክዋን ገድሎ አስተዳደርዋ እንዲዳከም የጀመረው መቅሰፍት እስከ አሁንም እየተባባሰ ቀጥሎ ህልውናዋን እየፈተናት ቢሆንም ፣ ዛሬ ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያናችን 50 ሚሊዮን የሚገመቱ አማንያን ፣ በርካታ የሃይማኖት አባቶች  ስባኪ መምህራን ፣ በተለያየ  ዘመናዊው የምዕራባውያን ትምህርት እስከ ዶክትሬትና ፍልስፍና ቢሰለጥኑም በሃይማኖታዊ ትምህርትም እስከ ዶክትሬት  በመማር ሃይማኖትን የሚታደጉ፣  በአንገታቸው ማህተባቸውን እስከ ሞት አስረው ጸንተው  የሚቆሙ  ፣  አጽዋማትን አምነው የሚጾሙ ፣  ስርዓተ ቅዳሴን ፣ ማህሌቱን ዝማሬውን  የሚያንቆረቁሩ ፣ ለጉባኤና ለታቦት ንግስ አገር አቋርጠው የሚጓዙ ፣  ሃይማኖት የሚሰራጩባቸው ሬዲዮና ቴሊቪዥኖች ። የተደራጉ ማህበሮች ፣  የሰንበት ትምህርት ቤቶች ፣ በገንዘብና በስልጣንም ከፍተኛ ቦታ ያላቸው አማኞች ያሉበት  ዘመን ከመሆኑም ባሻገር  በደረሰባቸው በደል ኦርቶዶክሳውያን በመላው ዓለም በመበተናቸው  ባሉበት ሁሉ ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን  በዓለም ከተሞች  እያበበች ፣ የሌሎች ሃገሮች  ዜጋዎችም  እምነቱን  እየተቀበሉ  ጋብቻቸውን በቅዱስ ቁርባን የሚፈጽሙባት ሆናለች ።

ሌሎች ለሚያምኑበት እምነት በማያውቁት ሃገርና ህዝብ ተጉዘው ገበተው  ቤተክርስቲያናቸውን ገንብተው  ፣ የሌሎች እምነት ተከታዮች ሳይቀሩ በጥሩ ምግባር ጥሩ ትምህርት ይሰጣሉ ብለው ልጆቻቸውን የሚልኩባቸው ከመዋዕለ ህጻናት እስክ ዩኒቨርስቲ የተሟሉ ትምህርት ቤቶች ፣ የጤና አገልግሎት የሚሰጡ የህክምና  ክሊኒክና ሆስፒታሎች ፣ ደካማ አቅም ላላቸው መደጎሚያ አገልግሎቶችና የነጻ የሙያና የትምህርት ዕድሎች  መፍጠር እንደቻሉ ሁሉ ኦርቶዶክሳውያንም ለኦርቶዶክሳዊ ተዋህዶ ተግባር /ORTHODOX TEWAHEDO MISSIONARY SERVICE/  ባለን ትልቅ አቅም  በርካታ ስራዎች ስራዎች የቤተክርስቲያናትን ህልውና መጠበቅና  ማስቀጠል በመሆኑ ፣  

  •  ነባር  የፈራረሱ ቤተክርስቲያናትን   እንዳይዘጉና እርዳታ እንዲጠናከሩ ማድረግ

  • ለእምነት ለአገልግሎትና ለካህናት የሚያስፈልግ ወጭ ለመሸፈን ዘላቂ የገቢ ምንጭ እንዲኖር ማገዝ፣

  • የምዕመናን ተዳከመው እንዳይጠፉና እንዲጠነክሩ   ኑሮ  የማሻሻያ ዕድሎች እንዲፈጠሩ  ካለን እውቅት በማካፈል  ማሳደግ፣  

  • ቤተ ክርስቲያን  እንደግል ቤታችን በንጽህና ተጠብቃ እንደ ጥንቱ ባማሩ የዛፍ ተክሎችና  ፍራፍሪዎች ማሳመር 

  •  በንግስና በጠበል ጉዞ ወቅት ቤተ ክርስቲያንና ምዕመናን  የሚለወጥ ስራዎችን  ይዞ የመስራት ልማድ  ማዳበር 

  • አዳዲሶች አማኞች እንዲመጡ ተጨማሪ አብያተ ክርስቲያናት  እንዲሰሩ ፣ ማድረግ

2 የቄስ ትምህርት ቤትን ማሳደግ  

ዘመናዊ ትምህርት ሲጀመር እንደማይጠቅሙ የተገፉት የቂስ ትምህርት ቤቶች በመቋረጣቸው ትውልዱ የኦርቶዶክስን አምልኮ ስርዓትና ስነምግባር  ክልጅነት ተቀርጽው የሚያዱጉበት ኧድልም ተዘግቶአል። ተተኪ ካልተዘጋጀ   አሁን ያሉት ታላላቅ ቤተክርስቲያናትም በምዕራቡ ዓለም ተተኪ በማጣት ወደ ቡና ቤትነትና ንግድ ድርጅት እንዳይቀየሩ ኦርቶዶክሳዊት ቢተክርስቲያናችንም በኦርቶዶክስ ስነምግባር ታንጸው ከዘመናዊ ትምህርት ጋር ተጣምሮ እንዲማሩ መሰረት ለመጣል የመጀመሪያው እርምጃችን የቄስ ትምህርት ቤቶች እንደገና በየቤተክርስቲያን እእንዲያብቡና ቀስ በቀስ እስከ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ደርሰው ለኦርቶዶክስ ዘብ የሚቆም ትውልድ ለማፍራት ፦  
⦁    ቤተክርስቲያናት ሁሉ  የቄስ ትምህርት ቤት  እንዲኖር  የመማሪያ ክፍል እንዲኖር ፣  ለአስተማሪ  ደሞዝ ፣  ለትምህርት መሳሪያዎች ድጋፍና   ማደራጀት
⦁     ከቂስ ትምህርት ቤት  ከሚያጠኗቸው ኦርቶዶክሳዊ  ጥናት ጋር የግዕዝን ትምህርት አብረው እንዲማሩና ቤተክርስቲያንዋን ስርዓት እንደልብ የሚከታተሉና በግዕዝ የተጥሽጻፉ መጻህፍትን  አንብበው በመረዳት ለሃገርም ጭምር  እንዲጠቅሙ  ወደ ዘመናዊ የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሲገቡም ሳይቋረጥ ድጋፍ እየተደረግላቸው  የጀመሩትን ትምህርት እንዳይረሱ ተከታታይ ትምህርት የሚያገኝበትን ማመቻቸት እጅግ ወሳኝ ይሆናል።

 ወጣቶች በተለያዩ ልማዶች ነጻ ሆነው ታላቅ የቤተ ሰብ ኃላፊ እንዲሆኑ ቀስ በቀስ  ኦርቶዶክሳዊ  አስተሳሰብና ምግባር በስርዓተ ትምህርቱ ሊካተቱ የሚችሉበት  የራሳችን የሆኑ የአንደኛ ፣ ሁለተኛ ደረጃና በሂደት እስከ ክፍተኛ ዩኒቨርስቲዎች ለማቋቋም  እስክንችል ወጣቶች ለቤተሰብና ለሃገር የመታዘዝ ፣ ታማኝ ዜጋ እንዲሆኑ  በእቅድ   ይዞ ማሳፋፋት ያስፈልጋል።  

3  የኔ ቢጤን /የጽድቅ በር

በቅዱስ ሉቃስ ወንጊል ምዕራፍ 16 ክቁ 19 - 31  የተጠቀሰው የሀብታሙ ሰውና አላዛር ምሳሌ ሁላችንንም አተኩረን ልንማረውና ልንተርጉመው የሚገባንን ታላቅ ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም አበክሮ እንድናደርገው የሚወደው ተግባር   በጣም አስበን መተርጎም ከቻልን ኦርቶዶክሳውያንን ወደ ትልቅ ደረጃ ያሻግረናል።  እኛ ጥሩ ለብሰን በሞቀ  በቤትክርስቲያን ውስጥ ተቀምጠን አስቀድሰን በጥሩ የተዘጋጀ  መክፈልት ቀምሰን ቤታችንም ገብተን በጥሩ ቤት የመኖርና የመመገብ ህይወት  እያለን ፣  ስንገባም ሆነ ስንመለስ  ብዙ ጊዜ እያለፍን አንዳንዴም  ትቂት ሳንቲም  ወይም ቁራሽ  ሰጥተን  አልፈናቸው የምንሄደውን  በተለምዶ " የኔ ብጤ" ብለን የምንጠራቸውን ምዕመናን ወገኖቻችን  ከተሰጠን ፋና የነሱንም ህይወት ደረጃ በደረጃ  ለመቀየር 

  • ከፀሃይ፣ ከዝናብና ብርድ ተገላግለው የሚቀመጡበት  ቦታ ከቤተክርስቲያኑ አጠገብ እንዲኖር ማገዝ   

  •  ለነሱ መለገስ ለጌታችን መለገስ ነውና ወደ ቤተክርስቲያን ስንሄ አስበን ይዘን በመሄድ  የምንሰጣቸውን  ምጽዋት ስርዓት ባለው መልክ እንዲያገኙ ማድረግ 

  •  ቤተ ክርስቲያን የሚሄዱት ለልመና በቻ ሳይሆን ቃለ እግዚአብሄርን እነሱም እንዲሰሙ  ማመቻቸት  

  •  ሕይወታቸው ሙሉ በልመና እንዳይሆን መስራት ለሚችሉ ባቅማቸው የስራ ዕድል መፍጠር   

  •  የተለያየ ሙያ እንዲማሩ ፣ ሙያዊና፣ የገንዘብ እገዝ አድርጎ ስራ እንዲሰሩ የሚያስችል  ልምድ በማዳበር ቤተ ክርስቲያናችንን በተጎሳቆሉ የኔብጤዎች የተከበበች  እንዳትሆን መስራት ይገባናል። 

4  ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ህጻናትና ልጆች እንከብካቤ

በየቤቱ ብዙ ወላጆች ልዩ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ልጆቻቸውን ይዘው መኖር ስለማይችሉ በመንገድ ላይ ይለቋቸውል።  ሰው ከልጁ በላይ የሚወደው ነገር የለም።   ጤነኛ ልጅ ማሳደግ  ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ልጅ ያለው ሰው ይረዳዋል። ለወላጆቹም ሆነ ለልጆቹ ከባድ መሆኑን እንዲሁም ይህን መካፈል በአምላክ ዘንድ ታላቅ ዋጋ ያስገኛልና  ትኩረት በመስጠት 


⦁    ልዩ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን ልጆች በፍቅር እንደ ልጆቻችን የማቅረብ ባህል ማዳበር
⦁    የሚመጥናቸው ዝግጅት በየዕድሜያቸው ማሳተፊያ መንፈሳዊ ዝግጅት እያቀረቡ በክርስቲያን ፍቅር መቅረጽ
⦁ በየመንገዱ ከመለመን እንዲወጡ  ባሉበት በቤተሰባቸው እርዳታ ማድረግና  ባላቸው አቅም ሊሰሩ የሚችሉትን ስራ እንዲሰሩ ማገዝዝ

5 ተከራይ ባልቤትና ገበሬውን  የተሻለ ባለቤት የማድረግ 


ለሰው ልጅ ቤት መኖር ታላቅ የሕይወት ደስታ መሆኑን የራስ ቤት ያለው ለመጀመሪይ ባለቤት ሲሆን ያለው ደስታ እጅግ ትልቅ መሆኑን    ዕድል ያገኙ ያውቁታል። በከተማም ሆነ  በገጠር  አብዛኛው ወገኖቻችን የሚኖሩባቸው ቤቶች በጣም አሳዛኝና የሃገራችንን የመጨረሻ ድህነትና ጎስቋላ ህይወት ያመለክታሉ። ለረጅም ዓመታት ብዙ የውጭ ረጂዎች እርዳት እያሉ ቢመጡም ችግሩ ምንም አልተነካም። ያገሩን ሰርዶ ባገሩ በሬ እንዲሉ በዚህ መልክ  ይህን መቀየር የሚያስችሉ እቅዶችና  ይዞ  ለመርዳት ጥረት መጀመር  ታላቅ ለውጥ ያስገኛል  ።

Donating is important

Help us building a new Shelter.