የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን
ኢትዮጵያ የሚለው ስም በኦሪት ዘፍ ከምዕራፍ 2፡ 13 ጀምሮ በብዙ ምዕራፎች ተጠቅሷል፡፡ ጥቂቱን ብንመለከት በኦሪት ዘፀዓት 2 ፡ 16 -22 ኢትዮጵያውዊው ካህን ታላቁን ነቢይ ሙሴን አስተናግዶ ልጁን ሲፓራን ድሮለት የተዋለደ እንደሆነ ፤ ንግስት ሳባ ልዩ ስጦታዎችን ይዛ ወደ ኢየሩሳሌም ባደረገቸው ጉዞ ከጥበበኛው ሰሎሞን ታላቅ ክብር ማኘትዋ፤ በሃዋርያት ስራ ም 8 ፡ 26-39 እንደተጠቀሰው፡ ኢትዮጵያዊው ጃንደርባ ኢየሩሳሌምን ተሳልሞ በመመለስ ላይ እንዳለ ቅዱስ ፊሊጶስ በመንፈስ ተልኮ ጃንደርባው የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን አዳኝነት አምኖ ተጠምቆ ፡ ጌታ በአረገ በዓመቱ በ34 ዓመተ ምህረት ክርስትናን ወደ ኢትዮጵያውያ ይዞ መለሱ ተመልክቷል። ኢትዮጵያውንም በቅድስት ሃገር ኢየሩሳሌም በጎልጎታ ነዋሪ ሆነው በማግኘትዋ ንግስት እሌኒ ጎልጎታን አሰርታ አራት መቅደሶችን እዚያ ለነበሩ ክርስቲያኖች ስታከፋፍል ፡ ከተሰሩት መቅደሶች ውስጥ ለኢትዮጵያውያንም እንደሰጠች በታሪክ መዛግብቶችና በጎብኝዎች ማስታወሻ ተጽፈዋል። በመሆኑም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በቅድስት አገር ኢየሩሳሌም ፡ በተለያዩ የእስራኤልና የፍልስጥኤም ግዛቶች ውስጥ 7 ገዳማትና የሚከራዩ ህንጻዎች ይዞታዎች አሏት፡፡
እነዚህን አሁን የሚያኮሩንን ገዳማት፡ ባለራዕይ በነበሩ የቀድሞ መሪዎችና አባቶች የተሰሩልን ቅርሶቻችን እንዳይጠፋብን ማንኛውንም የሚደርስባቸውን ግፍ ሁሉ ችለው ያቆዩልን ህይወታቸውን ለእግዚአብሄር አሳልፈው በሰጡ ጥቂት የገዳማቱ መነኮሳት አባቶች ትግልና መስዋእትነት ነው ።
ቅድስት ሃገር ኢየሩሳሌምን መጎብኘት የሁሉም ህልም ሲሆን አምላክ ፈቅዶ ለመጎብኘት የሚመጡ ሁሉ በመጽሃፍ ቅዱስ ሲነበቡ የነበሩ ቦታዎችን በአጭር የጉብኝት ጊዜ ለማዳረስ ሩጫ በመሆኑ የሚይዙትንና የሚጨብጡትን አሳጥቶ ያሰክራል፡፡ የመንፈሳዊ ቦታዎቹም በተለያዩ ቤተ እምነቶች (በግሪክ ፡ በካቶሊክ በመሳሰሉት) የሚተዳደሩ በመሆናቸው ለጥቂት ሰዓታት ጎብኝቶ መውጣት ስለሚሆን ፤ እረጋ ብሎ እንደፈለጉ መቆየትና መጸለይ የሚቻለው የራስ ይዞታ በሆኑት ገዳማት መሆኑን በኛ ይዞታ ስር ባሉን ገዳማት ወገኖቻችን አስተናግደውን ሙሉ የቅዳሴና የጸሎት አገልግሎቶችን የፈልገንን ያህል ሰዓት ተቀምጠን ስንገለገል የምናገኘውን ደስታና እርካታ ዕድሉ ገጥሞት ኢይሩሳሌምን የተሳለመ ሁሉ ይገነዘበዋል።
እንኩዋንስ በአንድ ጊዜ ጉብኝት ቀርቶ ብዙ ጊዜም ቢመላለሱ ከገዳሙ አባቶች ጋር ጊዜ ወስዶ በበቂ ጊዜ ተቀምጦ መወያየት የሚቻልበት አጋጣሚ ስለሌለ ፡አብዛኛዎቹ ጎብኚዎች ስላሉን ገዳማት በቁ ግንዛቤና ዕውቀት ሳያገኙ ይመለሳሉ።
እስካሁን ሄደው በሙሉ ሳያውቁት ለተመለሱ ፤ወደፊት ለሚሄዱና ባይሄዱም ካላቸው ጽኑ የቤተክርስቲያናትና ገዳማት ፍቅር ባሉበት ሆነው የበረከቱ ተሳታፊ በመሆን የገዳማትና የቤተክርስቲያን ህልውና ለማስጠበቅ ለሚጥሩ ምዕመናን ሁሉ በእስራኤልና ፍልስጥኤም ግዛቶች ስላሉን የኤትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ገዳማትና ህንጻዎች ያወቁትንና የተረዱትን ያህል በማቅረብ ከምዕመናንና ከገዳሙ ማህበር ጋር የመቀራረብ ዕድል ፈጥሮ ሁሉም ባለው አቅም በመሳተፍ ቅርሶቻችንን እንድናጠናክራቸው ይረዳ ዘንድ ከአጭር የጽሁፍና የፎቶግራፍ መግለጫዎች ጋር በቅደም ተከተል ቀጥሎ ቀርበዋል።
የገዳማቱ ዝርዝር ፡አጭር ታሪክና የፎቶግራፍ መግለጫዎች
1. ዴር ሱልጣን ገዳም በ320 ዓ ም/ በኢየሩሳሌም አሮጌው ከተማ ውስጥ ጎልጎታ ጌታችን መቃብር አጠገብ/
2. ደብረ ገነት ገዳም በ1850 ዓ ም የተመስርተ / በኢየሩሳሌም ከተማ ውስጥ የሚገኝ/
3. ቅዱስ ፊሊጶስ ገዳም በ 1883 ዓ ም የተሰራ ኢየሩሳሌም በአሮጌው ከተማ ውስጥ የሚገኝ /
4. ቅድስት ሥላሴ ገዳም በ1915 ዓም /የተሰራ በዮርዳኖስ ወንዝ ዳር የሚገኙ/ አሁን ኢያሪኮ ድርብ/
5. ቅዲስ ገብርኤል ገዳም በ1920 ዓ ም/ ኢያሪኮ ከተማ /ገዳመ ቆሮንቶስ አጠገብ
6. ምስካነ ቅዱሳን ዓልዓዛር ገዳም በ1945 ዓ ም/ ቤታንያ/አላዛር መቃብር አጠገብ/
7. ቤተልሄም ገዳም በ1982 ዓ ም/ ቤተልሄም ጊታችን በተወለደበት አጠገብ
8. ሌሎች ህንጻዎች
Lorem ipsum dolor sit amet, consectetur adipisicing elit. Veritatis, dolorem!
Lorem ipsum dolor sit amet, consectetur adipisicing elit. Veritatis, dolorem!
Help us building a new Shelter.