Bete Giorgis the mythical Lalibela church


Church Of Our Lady Of Zion In Axum Ethiopia


Jesus sefer for us!


Jesus sefer for us!


Debre Genet Ethiopian Orthodox Church in Jerusalem


Debre Mihret St.Michael Ethiopian Orthodox Tewahedo Church in Wheaton, IL


Ethiopian Orthodox


Holy Trinity Cathedral, an Ethiopian Orthodox church building in Addis Ababa.


Axun Zion 

                                                                      በቅድስት አገር ኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት

ኢትዮጵያ የሚለው ስም በኦሪት ዘፍ ከምዕራፍ 2፡ 13 ጀምሮ በብዙ ምዕራፎች ተጠቅሷል፡፡ ጥቂቱን ብንመለከት በኦሪት  ዘፀዓት 2 ፡ 16- 22  ኢትዮጵያውዊው ካህን ታላቁን ነቢይ ሙሴን አስተናግዶ ልጁን ሲፓራን ድሮለት የተዋለደ እንደሆነ ፤ ንግስት ሳባ ልዩ ስጦታዎችን ይዛ ወደ ኢየሩሳሌም ባደረገቸው ጉዞ ከጥበበኛው ሰሎሞን ታላቅ ክብር ማኘትዋ፤ በሃዋርያት ሥራ ም 8፡26-39 እንደተጠቀሰው፡ ኢትዮጵያዊው ጃንደርባ ኢየሩሳሌምን ተሳልሞ በመመለስ ላይ እንዳለ ቅዱስ ፊሊጶስ በመንፈስ ተልኮ ጃንደርባው የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን አዳኝነት አምኖ ተጠምቆ ፡ ጌታ በአረገ በዓመቱ በ34 ዓመተ ምህረት ክርስትናን ወደ ኢትዮጵያውያ ይዞ መለሱ ተመልክቷል። ንጉስ ቁስጠንጢኖስ ክርስትናን ሕጋዊ ካደረገ በሁዋላ እናቱ ንግስት እሌኒ ኢትዮጵያውን በቅድስት ሃገር ኢየሩሳሌም በጎልጎታ ነዋሪ ሆነው በማግኘትዋ  ጌታችን ተሰቅሎ የተቀበረበትን ጎልጎታን አሰርታ  እዚያ ለነበሩ ክርስቲያኖች ስታከፋፍል ፡ ከተሰሩት መቅደሶች ውስጥ ለኢትዮጵያውያንም እንደሰጠች በታሪክ መዛግብቶችና  በጎብኝዎችም ማስታወሻ ተጽፈዋል።  በጥንት አባቶቻችን የሃይማኖት ጽናትና በአማኝ ነገስታት ድጋፍ  ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተወለደበት በቤተልሄም ፣ በተጠመቀበት በዮርዳኖስ ፣ 40 ቀን ጾሞ በጸለየበት በገዳመ ቆሮንቶስ  አጠገብ በኢያሪኮ ፣ አልአዛርን ከሞት ባስነሳበት በቢታንያ፣ ተሰቅሎና ተወግሮ ሞትን ድል በነሳበት በጎልጎታ ውስጥና በኢየሩሳሌም ከተማዎች በጠቅላላው 7 ገዳማት አሏት።

እነዚህን አሁን የሚያኮሩንን ገዳማት፡ ባለራዕይ በነበሩ የቀድሞ መሪዎችና አባቶች የተሰሩልን ቅርሶቻችን እንዳይጠፉብን ማንኛውንም የሚደርስባቸውን ግፍ ሁሉ ችለው ያቆዩልን ህይወታቸውን ለእግዚአብሄር አሳልፈው በሰጡ ጥቂት የገዳማቱ መነኮሳት አባቶች ትግልና መስዋእትነት ነው ።  ቅድስት ሃገር ኢየሩሳሌምን መጎብኘት የሁሉም ህልም ሲሆን አምላክ ፈቅዶላቸው ለመጎብኘት የሚመጡ ሁሉ በመጽሃፍ ቅዱስ ያነበቧቸውን ቦታዎች ለማዳረስ ሩጫ በመሆኑ ስለገዳሞቻችን ለማወቅ ጊዜ አይበቃም፡፡ አብዛኛዎቹ መንፈሳዊ ቦታዎች  በተለያዩ ቤተ እምነቶች  የሚተዳደሩ በመሆናቸው ለጥቂት ሰዓታት ጎብኝቶ መውጣት  ነው።  እረጋ ብሎ እንደፈለጉ መቆየትና መጸለይ የሚቻለው የራሳችን ይዞታ በሆኑት ገዳሞቻችን  መሆኑን  ወገኖቻችን አስተናግደውን ሙሉ የቅዳሴና የጸሎት አገልግሎቶችን ፣የፈለግንውን ሰዓት ቆይትን  የምናገኘውን ደስታና እርካታ ዕድሉ ገጥሞት ኢይሩሳሌምን የተሳለመ ሁሉ ይገነዘበዋል። 
እንኩዋንስ በአንድ ጊዜ ጉብኝት ቀርቶ ብዙ ጊዜም ቢመላለሱ ከገዳሙ አባቶች ጋር ጊዜ ወስዶ በበቂ ጊዜ ተቀምጦ መወያየት የሚቻልበት አጋጣሚ ስለሌለ ፡አብዛኛዎቹ ጎብኚዎች ስላሉን ገዳማት በቂ ግንዛቤና ዕውቀት ሳያገኙ ይመለሳሉ።   እስካሁን ሄደው በሙሉ ሳያውቁት ለተመለሱ ፤ወደፊት ለሚሄዱና ባይሄዱም ካላቸው ጽኑ የቤተክርስቲያናትና ገዳማት ፍቅር ባሉበት ሆነው የበረከቱ ተሳታፊ በመሆን የገዳማትና የቤተክርስቲያን ህልውና ለማስጠበቅ ለሚጥሩ ምዕመናን ሁሉ በእስራኤልና ፍልስጥኤም ግዛቶች ስላሉን የኤትዮጵያ ኦርቶዶክስ  ገዳማትና ህንጻዎች ያወቁትንና የተረዱትን ያህል  በማቅረብ ፣ ከምዕመናንና ከገዳሙ ማህበር ጋር የመቀራረብ ዕድል  ፈጥሮ ሁሉም ባለው አቅም በመሳተፍ ቅርሶቻችንን እንድናጠናክራቸው ይረዳ ዘንድ ከአጭር የጽሁፍና የፎቶግራፍ መግለጫዎች ጋር  በቅደም ተከተል ቀጥሎ ቀርበዋል።


Donating is important

Help us building a new Shelter.