በኢትዮጵያ 

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን 

                     በኢየሩሳሌም


በቅድስት አገር ኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት

በቀረው ዓለም

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን

በቀረው ዓለም ሃገሮች

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን 

Lorem ipsum dolor sit amet, consectetur adipisicing elit. Veritatis, dolorem!

Lorem ipsum dolor sit amet, consetetur.

Lorem ipsum dolor sit amet, consectetur adipisicing elit. Veritatis, dolorem!

Lorem ipsum dolor sit amet, consetetur.

Lorem ipsum dolor sit amet, consectetur adipisicing elit. Veritatis, dolorem!

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን 

L

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን 


 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በኢትዮጵያና በመላው ዓለም በርካታ ቤተ ክርስቲያናት፣ ገዳማትና ምዕመናን አሏት።  አምልኮተ እግዚአብሄር ፡ በአስተዳደራዊ ፡ ፍትሃዊነት፡ ለዕምነት ጽናት ፡ በረሃና ውቅያኖስ አቆርጦ ለእምነት መሞት ፣ ከራስ ጥቅም ይልቅ ሃብትና ንብረትን ለዕግዚአብሄር የማዋል ምግባር  በአባቶቻችን አኩሪ መሰረት የነበረን መሆኑን ፡ በቅዱሳት መጻሕፍትም ተጠቅሰዋል።

በዘመነ ብሉይ፡

  •  ደገኛው የምድያም ካህን ራጉኤል/ዮቶር /ያለምንም ጥቅም  ፍለጋ ታላቁን ነቢይ ሙሴን አስጠግቶ ፥ህይወቱን አትርፎ፣ ልጁን ኢትዮጵያዊትዋን ሲፓራን ድሮለት ሁልት ልጅ እንደወለደችለት፣ በኦሪት ዘጸዓት ም 2፡ 16– 22 ና በኦሪት ዘኁልቁ ም 12፡1 

  • ኢትዮጵያዊው የንጉስ ባለሟል አቤሜሌክ ስልጣኑንና ህይወቱን ሊያሳጣው የሚችል ቢሆንም ለዕውነት  በመቆም ቆራጥ አቋም ወስዶ ፤ የነቢዩ ኤርምያስን ህይወት ከሞት ማዳኑን በትንቢተ ኤርምያስ ም 38 ፡ 7 – 13 

  • ንግስተ ሳባ እግዚአብሔር ለሰለሞን  የሰጠውን ጥበብና ዕውቀት በአካል ተገኝታ ለማየት በዚያን ዘመን ወደ ቅድስት አገር ኢየሩሳሌም ስትሄድ” ለንጉሡም መቶ ሀያ መክሌት ወርቅ እጅግም ብዙ ሽቱ የከበረም ዕንቁ ሰጠችው  ፣ የሳባ ንግሥት ለንጉሡ ለሰሎሞን እንደ ሰጠቸው ያለ የሽቱ ብዛት ከዚያ ወዲያ አልመጣም ነበር “ ተብሎ ተመዝግቧል ። መጽሃፈ  ነገስት  ቀዳማዊ  ም ፡ 10 ቁ 1-10

በዘመነ ሀዲስ፡ 

  • በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ  8 ቁ 26-39 ኢትዮጵያዊው  ጃንደርባ ኢየሩሳሌምን ተሳልሞ  የነቢዩ ኢሳይያስን ትንቢት እያነበበ ሲመለስ በመንፈስ ቅዱስ በተላከው  ሐዋርያው ቅዱስ ፊሊጶስ  ተጠምቆ ክርስትናን  በ34 ዓመተ ምህረት  ኢትዮጵያ  አስገብቷል።

  • በኢትዮጵያ ነገስታት ከቤተ መንግስት እስክ ታች ባለው ሕዝብ በይፋ ክርስትና ከ330 ዓመት ምህረት  ጀምሮ  በሰላም  የተስበክባትና  ጥንታዊ ከሚባሉት አንዷ ስትሆን ከሮምና ሶርያ  በአረመኔ ነገስታት ከሚደርስባቸው ጥቃት  ሸሽተው የመጡ አባቶችንም ተቀብላ  በሰላም ኖረው አስተምረው በስማቸው ቤተክርስቲያን ተሰይሞ እስከ አሁንም ይዘከራሉ።

  • እንደ ቅዱስ ያሬድ ያሉ ምጡቅ የዜማ ፣ የሥነ ጥበብ አዋቂዎች ፣በራስዋ  ቋንቋ በግዕዝ የተጻፉ የዜማና ፣ ቅኔ፤ የስሥነ ፈለግ ፣ ሥነ ህንጻ ፤  መድሃኒት፣  የተለያዩ የጸሎት መጻህፍትና ፣ ዓለም ለትክክለኛ መረጃ  ቅርስነት የመዘገበው በግዕዝ የተጻፈ ኢትዮፒክስ በለው የሚጠቀስ መጽሐፍ ቅዱስ  አሏት።

  • በህገ ልቡና  ከካም ፣ ኦሪትን ከንጉስ ሰለሞን ልጅ ቀዳማዊ ምኒልክ  መምጣት ጀምሮ  ለሺህ ዓመታት ፣ አዲስ ኪዳንን  ከ34 ዓ፣ ም ጀምሮ አምላክ የተመሰገነባት  ቅድስት ሃገር ኢትዮጵያ በአክሱም የሙሴ ጽላትና በግሼን  ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደሙን ያፈሰሰበት  የኢየሱስ ክርስቶስ ግማደ መስቀል  ይገኛል ።

  • ዓለምን የሚያስገርመው የቅዱስ ላሊበላ ቤተክርስቲያናት፡ የጣናና ሌሎች በርካታ ድንቅ ቤተክርስቲያናትና  ገዳማት በብዛት አሉ።

  • ከቤተክርስቲያናትና ገዳማት ጋር የተጣመሩት የአብነት የትምህርት ቤቶችዋም በግዕዝና በቅኔ የበለጸጉ  ካህናት፣ ዲያቆናትና መምህራን ያወጣሉ።

  • የእስልምና እምነት ሲጀመር ነቢዩ መሃመድ የፍትህና የነፃነት ሃገር ወደ ሆነቸው ኢትዮጵያ በስደት የላኳቸው ተከታዮቻቸው በሰላም  ኖረው ለእስልምና እምነት መሰረት ሆና  የአብሮነት ባህል ዳብሮባታል።

የቤተክርስቲያንዋ ፈተናዎችና፣  ጽናት 

  • በተለያየ ዘመናት በተነሱት በዮዲት ጉዲት ፣ የክርስትናውን ዓለም ባንቀጠቀጠው በኦቶማን ቱርክ አጋዥነት በተነሳው በሃገር በቀሉ ግራኝ መሐመድ፣ በፋሽስት ኢጣልያ  ወረራዎችና  በ1960ዎቹ በሃገራችን የተጀመረው የማርክሳዊ አስተሳሰብ መንግስትን ማናጋት ብቻ ሳይሆን በሃይማኖት ጠልነቱ፣ የዘርና የሃይማኖት አክራሪነት በማስረጹ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የጥቃት ኢላማ ተደርጋ ቤተክርስቲያናት ፣ ገዳማት ፣ንዋየ ቅድሳትና መጻህፍት  በእሳት እንዲጋዩና  እንዲዘጉ ፡ ካህናቶች ፡ ዲያቆናትና  ምዕመናን  በአሰቃቂ ሁኒታ እንዲታረዱ ቢደረግም  በአማኞችዋ ጽናትና በእግዚአብሄር ድጋፍ  በየጊዜው በሚያስነሳቸው   አቡነ ተክለሃይማኖትን የመሳሰሉ ታላላቅ የወንጌል አምዶች አባቶች  ፣ እስክዛሬ ዓለምን የሚያስገርሙን ቤተ ክርስቲያናትን የቀረጹትን ቅዱስ ላሊበላን በመሰሉ ነገሥታት ፣ ተውልድ ተሻጋሪ  እውቀትና የቤተክርስቲያን ወርቃማ ዘመን ያሰኙ እነአጼ ዘርዓ ያዕቆብን መሰል መሪዎችና  በጠንካራ የማኞችዋ ጽናት እስካሁንም ወደፊትም ትቀጥላለች 

  • ጥንታዊ የነበሩትን አብያት ክርስቲያናት ዛሬ ያሉበንት ሁኔታ በጥቂቱ ስንመለከት

    • እነቅዱስ ዮሐንስና ቅዱስ ጳውሎስ ያስተማሩባቸው ፣ በዮሐንስ ራዕይ በምዕራፍ 2 ና 3  የተጠቀሱት 7ቱ የመጀመሪያው ምዕተ ዓመት ቤተ ክርስቲያናት ከተሞች ( ኤፌሶን ፣ ስምርኔስ ፣ ጴርጋሞን ፣ ትያጥሮን ፣ ሰርዴስ፣ ፌላድልፊያና ሎድቅያ) የክርስቲያኖች ቁጥር ከግማሽ ሚሊዮን በታች እጅግ አንሶ በዛሬዪቱ ቱርክ ቦታና መብትም የላቸውም። 

    • ታላቁ ቁስጠንጢኖስ ከጣዖት አምልኮ ነጻ የሆነች አዲስ ንጹህ ከተማ ብሎ የቆረቆራት የኮኒስታንቲኖፕል ከተማ ዛሬ ስሟ  ኢስታንቡል ተብላ የክርስቲያን ዝናዋ ሲወድም  ሃጌ ሶፍያ ብሎ በወርቅ ያሰራት  ልዩ ቤተ ክርስቲያን በኦቶማን ቱርክ  የ1453 ዓመት ምህረት ድል ፣ ወርቋ ተዘርፎ  ወደመስጊድነት ተቀይራ ስትኖር ቆይታ በ1935 ወደ ሙዚየምነት  ተቀይራ በሁሉም  ስትጎበኝ  በ2020 ዓመተ ምህረት በድጋሚ ወደ መስጊድነት ተቀይራ በሙዚየምነት እንኳን በክርስቲያኖች መጎብኘትዋ ቀርቷል።  

    •  የቅዱስ ማርቆስ መንበር ይገኝባት የነበረችው የግብጽዋ አሌግዛንደሪያ  በዓለም የነበራት ከፍታዋ ተንዶ ጥቂት  ክርስቲያኖች ሲቀሩ፣ እነሱም አዲስ ቤተክርስቲያን  የመስራት ፣ ነባሮችን  ማደስና በመንግስት ስራዎች ለመካተት እንዳይችሉ ከፍተኛ ተጽዕኖ ይደረግባቸዋል

    •  የቅዱስ ጳውሎስ የስብከት መጀመሪያው ደማስቆ የሚገኝባት ሶርያ ታላላቅ የአብያተ ክርስቲያናቶችና ቅርስ የነበረባት አሌፖ ከተማ ባለፉት 10 አመታት በእርስ በርስ ጦርነት ስትወድም  ዓለም እያያቸው አላዳናቸውም ። ተመናምነው የነበሩት የተዋህዶ ኦርቶዶክሳውያንም ጭራሹን ተመናምነው  በአጠቃላይ የሃገሪቱ ህዝብ ላይም አሳዛኝ ጉዳት ደርሷል ። ከጦርነቱ በፊት በሶርያ ከነበረው አብዛኛው በነበረበት ቤት አይኖርምም።  በሃገር ውስጥ ተፈናቃይ ሆኗል፣ ብዙዎች መሰደዳቸውና በንበረት ላይ የደረሰው ዘግናኝ የውድመት ሰቆቃ ጆሮ ላለው ትልቅ ደወል ነው። በግልጽ ክርስቲያኖች ሲታረዱ ፣ ሲፈናቀሉ ፣ ከተማቸው እንዳለ በእሳት ጋይቶ ሲወድም  የመላው ዓለምም የእርሱ ፍላጎት ከሌለበት ሃገሮች ሲወድሙ በህዝብ ላይ ሰቆቃ ሲፈጸም እያየም አያይም። እየሰማም አልሰማም፣ እንደሩዋንዳ ወደፊት የፌዝ ይቅርታ ይል ይሆናል። 

    • አንድ የነበረችው ቤተክርስቲያን በ451 ዓመተ ምህረት በአራተኛው የኬልቆዶን ጉባኤ ስትከፈል የጥንቱን  የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት አንቀይርም ያሉት /ኦሪዬንታል ኦርቶዶክስ/ በመባል የሚታወቁት 6ቱ  እህትማማች አብያተ ክርስቲያናት (እትዮጵያ  ፣ ግብፅ ፣  አርመን፣ ሶርያ ፣ ህንድና ፣ ኤርትራ) ዛሬ  80 ሚሊዮን ሲገመቱ ከዚህም  በኢትዮጵያ 50 ሚሊዮን 10 ሚሊዮን በግብጽ 20 ሚሊዮን የሚሆኒት በቀሩት ሃገሮችና አማኞቻቸው ተሰደው  ባሉበት የዓለም ሃገሮች  ይገኛሉ። 

  • ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያናችንም እየገጠማት ያለውን የህልውና ጥቃት ፣ የምዕመናኑ በኤኮኖሚ መዳከም የሌሎቹ እጣ እንዳያጋጥማት ሌላ ከውጭ የሚረዳት ስለሌለ በሃገርና በመላው ዓለም የምንገኘው ኦርቶዶክሳውያን ከህልውና ጥቃት እንድትጠበቅ፣ ያሉት አማኞችዋም ተጠናክረው  ሌሎችም እየተጨመሩ  እንዲከተሏት የኦርቶዶክሳዊ ተዋህዶ ተግባር አገልግሎት /ORTHODOXIAN TEWAHEDO MISSIONARY SERVICE/ ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 5፡ ቂ 13 ፟-16  እናንት ጨውና ብርሃን ናችሁ ብርሃናችሁ ሌሎችም ይብራ  ብሎ  ባስተማረን መሰረት እርሱ ወደ አዘጋጀልን ስማያዊት ኢየሩሳሌም ለመውረስ በምንችለው ሁሉ እንድንንቀሳቀስ  የመነኩሴ ድህረ ገጽን በማዘጋጀት በኢትዮጵያ ፣ በቅድስት ሃገር ኢየሩሳሌምና በተቀረው ዐለም ስላሉን ቤተክርስቲያናትና ገዳማት አውቀን እንድንረዳ ፋና በኢትዮጋት /FabaBEthioGat / በሚል የስራ ርዕይ  የመነሻ የተግባር መርሃ ግብር ዝርዝሮች አይታችሁ  ፣ ሃሳባችሁንና  ተሳትፏችሁን አጋሩን  አብረን ለቤተክርስቲያናችን እንስራ.

Donating is important

Help us building a new Shelter.