የመነኩሴ ጽንስ ሃሳብ በጥቂቱ
መነኩሴ ጠቅላላ ህይወቱን ለእግዚአብሄር የሰጠ ፡ በፈቃደኝነት እራሱን ደሃ በማድረግ ለምንም ዓለማዊ ኑሮ ፡ ገንዘብ ፡ ምቾትና የግል ጥቅም ሳይደለል ለዓለም ሁሉ ሰላም በመጸለይ ለበጎ ስራ ቃል ኪዳን የገባ በሁሉም የታመነ የቤተክርስቲያን ቅን አገልጋይ ማለት ነው፡፡ የመለኩሴም ጽንሰ ሃሳብ የተወለደው የነዚህን መነኩሴዎች የበጎ ስራ ጽናትና ራዕይ በመከተል በቀና መንፈስ ህብረተሰብን በማነቃቃት፤ ከቤተክርስቲያን ጎን ተሰልፎ ያለውን ዕውቀትና ገንዘብ በማካፈል ጥንታዊና ታሪካዊ ቤተክርስቲያናችንን ለመጠበቅና ለማሳደግና በቅድስት አገር ኢየሩሳሌም ያሉንን ገዳማት ህጋዊ መብት አስከብሮ ለመርዳትና ለሰው ልጆች ህይወት በሚቻለው ሁሉ ለመርዳት ነው፡፡
A Bit of Background
Menekuse is the Amharic word for a monk. A Menekuse is an individual who is totally dedicated to God, takes the vows of poverty, chastity and obedience. They serve the church with dedication, work for the salvation of the world, and give their lives to charity work. The vision of Menekuse is born out of the lives of these dedicated Menekuses. Our vision is to empower communities by partnering churches, imparting vision to the next generation, and bring together people to preserve the Ethiopian churches and support our monasteries in Jerusalem.